የትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር የመፍታት ጉዳይ የሁሉም ኃላፊነት ነው አሉ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ
ይህን ያሉት የዞኑ ትምህርት መምሪያ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 25ኛው የትምህርት አስተዳደር ጉባዔ ላይ ነው።
ጥቅምት 10/2018 ዓም፡-ስልጢ ወረዳ ኮመኒኬሽን
የትምህርት ጥራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ 25ኛውን የትምህርት አስተዳደር ጉባዔውን በወራቤ ከተማ አካሂዷል፡፡
በዚሁ ወቅት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንዳሉት ትምህርት ብቁና በቂ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው።
ይህንኑ ለማሳካት ባለፉት ዓመታት የትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ አግባብነትና ጥራትን ለማጎልበት ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲሆ የትምህርት ጥራትን በተመለከተ በተለይ የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል አኳያ ችግሮች ይስተዋላሉ ብለዋል።
በመሆኑም ከችግሩ አንገብጋቢነት አኳያ ባለድርሻ አካላት ሁነኛ ምላሽ መስጠት የዘርፉ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተረድተው በሙሉ አቅም ሊተጉ ይገባል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዘይኔ አሳስበዋል።