የስልጢ ወረዳ አስተዳደር ለቀድሞው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ለነበሩት ለአቶ ከድር ደድገባ የሽኝት መርሃ-ግብር አካሄደ!
ነሃሴ 16/2017 የስልጢ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
የስልጢ ወረዳ አስተዳደር ለቀድሞው ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ደድገባ የሽኝት መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ረዲ የቀድሞው ዋና አስተዳደር አቶ ከድር በወረዳው በዓመታት ቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።
ወረዳውን ሲያስተዳድሩ በነበሩበት ወቅት በርካታ የልማት ተግባራትን ማከናወናቸውንና በወረዳው ውስጥ መልካም የስራ ተነሳሽነት መፈጠሩንም ያነሱት አቶ ሸምሴ።
የቀድሞው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የአሁኑ የስልጤ ዞን ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ደድገባ ወረዳው ላደረገላቸው ሽኝት ያመሰገኑ ሲሆን እንደ ወረዳ የተጀመሩ ተግባራት ከአሁኑ ዋና አስተዳዳር ጋር በጋራ በመሆን በተሻለ ተነሳሽነት እንደሚፈጸሙ ያላቸውን እምነት አስቀምጠዋል።
በስልጢ ወረዳ ውስጥ የተከናወኑና እና እየተከናወኑ ያሉ ጥቅል አፈጻጸሞች ውስጥ የሁሉም የወረዳው አመራርና ማህበረሰብ ሚናና አሻራ ከፍተኛ እንደነበር አቶ ከድር ተናግረዋል።
የስልጢ ወረዳ አጠቃላይ አመራር አካላትም መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው በድጋሚ ተመኝቷል።
