የስልጢ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሴቶች ክንፍ ህብረት ኮንፈረንስ መድረክ ተካሄደ።
ጥቅምት 11/2018 ስልጢ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን
____
በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ህብረት ኮንፈረንስ መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ሩብ ዓመት በሴቶች ክንፍ መሪነት የተከናወኑ ተግባራት፣ የተገኙ ስኬቶችንና ተግዳሮቶችን ለይቶ በማወቅ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር አይተኬ ሚና ያለው ስለመሆኑም ተመላክቷል።
አባላትን ማጠናከር፣ ዕጩ አባላትን ማፀደቀ፣ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ማድረግ፣ ከትምህርትና ከጤና ጋር፣ ከስራ አጥ ለይታ እንዲሁም ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ከሴት ፐብሊክ ሰርቫንቱ ጋር ምክክርም ተደርጓል።
በሩብ ዓመቱ በፓርቲው እየተመዘገቡ ያሉ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ተግባራቶች ዕውን እንዲሆኑ የሴቶች የህብረት እና የብልጽግና ቤተሰብ በማጠናከር የብልፅግናን ጉዞን ማፋጠን ይገባል ሲሉ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወይዘሮ በህሪያ ረዲ ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አደረጃጀት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የሴቶችን ተሳትፎ ለመጨመርና ፓርቲው ያስቀመጠዉን ግብ ለማስፈፀም የተከናወኑ ተግባራትን ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ከአባላቱ ጋር በመሆን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ስኬቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል ተግዳሮቶችን ደግሞ ለማረም የኮንፈረንስ መድረኩ ጉልህ ሚና እንዳለው ኃላፊዋ ገልፀዋል።