siltiworeda

ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማህበረሰቡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባሻገር የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው የስልጢ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ!

ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማህበረሰቡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባሻገር የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው የስልጢ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ!
ነሐሴ 14/2017/ ስልጢ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ማህበረሰቡን በቴክኖሎጂ የተደገፈ እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባሻገር የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ስርጋጋ አስታውቀዋል።
የወረዳው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ስርጋጋ እንደ ወረዳ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በተመለከተ ለወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጡት መረጃ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግስት ከአረብ ኤሚሬትስ መንግስት ጋር በመተባበር 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ተጠቃሚ እንዲሆን ባመቻቸው እድል በወረዳ ደረጃ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ፣
በድጅታል ሊትሬሲ (በዳታ ሳይንስ) ፣
በፕሮግራሚንግ ፣ በአንድሮይድ ልማት እና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች በ2017 እስከ ሰኔ 30 ባለው 821 የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ስልጠናው አጠናቀው ሰርቲፋይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለውም የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ራስን በዲጅታል እውቀት ብቁ በማድረግ ረገድ ሚናው የላቀ በመሆኑ የሀገራችን ህብረተሰብ በተለይም ወጣቱ ክፍል ለስልጠናው ትኩረት በመስጠት ስራ መፍጠር እንደሚችል ተናግረዋል።
ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ስልጠናውን መውሰድ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው አጠቃላይ በወጣቱ ዘርፍ፣ምሁራን፣ተማሪዎች እና አመራር አካላት በድጋሚ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም በያዝነው በጀት ዓመት የክረምት በጎ ተግባርን መሰረት ያደረገና እንዲሁም ከተማሪ ቅበላ ጋር የተማሪዎች ኢትዮኮደርስ ምዝገባ ከ8ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቱ ተመዝግበው ሰርቲፋይ እንዲሆኑ የክልል እና የዞን አቅጣጫ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ባለድርሻ አካላት ተግባሩን በአጽንዖት እንዲመሩት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *